ፍቅር ገደለ አሉ የወደደዉን
እሱን ማን አስታሞ ሊቀብረው ይሆን
እንጀራ አልፈልግም ምን ያደርግልኛል
ትዝታውን ይዤ ልሂድ ይበቃኛል
የዚያ ማዶ ሰዎች ዘፈን አያምራቸው
አጅሬ ትዝታ አልገባም ቤታቸው
ፍቅርን ጨርሼው ከመጣሁ በሗላ
ትዝታ ረበሸው ምነው የኔን ገላ
ይህ ትዝታ ሚሉት ናፍቆት ነው በሽታ
ቀኑስ ይታለፋል አይችሉትም ማታ
ብፈልግ ባልፈልግ ብወደው ባልወደው
ብወድም ባልወድም አይጠፋም ከጎኔ
የትዝታ ደብር ገዳሙ ነኝ እኔ
ከፊቴ እየቆመ የሰው ስጋ ለብሶ
እውነት ነው ወይ ቅዠት አቃተኝ ጨርሶ
ደግ ደጉን ሳጣ ሀዘኔ መረረ
ሞትን ሞት ቢወሰደዉ ይሻለኝ ነበረ
it's not about being inseparable; it's all about being separated and nothing changes
I love this song
gtzaman 2 months ago