Alert icon
We're changing our privacy policy. This stuff matters.  Learn more  Dismiss

ሐል ፋር የመጠለያ ጣቢያ፣ ማልታ

Loading...

Sign in or sign up now!
Alert icon
Upgrade to the latest Flash Player for improved playback performance. Upgrade now or more info.
1,308
Loading...
Alert icon
Sign in or sign up now!
Alert icon

Uploaded by on Feb 21, 2011

በሱዳን በረሃ ተጉዘው የሰሐራን በረሐ እንደ ግመል ያቋርጣሉ፡፡ ረሃቡ፣ ጥማቱ በትግል እና በወኔ ይታለፋል፡፡

በየመንገዱ መኪና ሲበላሽ መቆሙ፣ ከፖሊሶች ለመደበቅ በየተራራው ሥር ከአንድ ቀን እስከ ለሁለት ሳምንት ያለ ምግብ መቀመጡ፤ በየቀኑ ብር ጨምሩ ከሚሉ አሻጋሪዎች ጋር መጨቃጨቁ የታለፍና ሊቢያ ይገባል፡፡

ከሊቢያ ፖሊሶች ተደብቆ፤ በማይታወቅ ቤት ውስጥ ከርሞ፣ በሌሊት ጀልባ ላይ ወጥቶ በሜዲትራንያን ባሕር ላይ ጉዞ ይጀመራል፡፡ በሕይወት እና በሞት መካከል እየተጓዙ፣ ከተሰበረ ኮምፓስ ጋር እየታገሉ፤ ልምድ በሌለው ካፒቴን እየተመሩ፤ በእግዚአብሔር ቸርነት ከባሕር አውሬ ተርፎ ማልታ ይገባል፡፡

ማልታ ላይ ደግሞ በፖሊስ ተይዞ መጀመርያ ወደ እሥር ቤት detention center ከዓመት እና ከሁለት ዓመት በኋላ ሲወጡ ደግሞ ወደ መጠለያ የድንኳን ካምፕ ይገባል፡፡ እሥር ቤቱ ዙርያው በግንብ እና በሽቦ የታጠረ ሲሆን አንዳንዶች እየዘለሉ፣ ሌሎች ዘመናቸውን ጨርሰው ወጥተው በአሁኑ ጊዜ ምንም አበሻ በውስጡ የለበትም፡፡

የመጠለያ ጣቢያው ውስጡ በኮንቴይነር እና በአረጁ ድንኳኖች የተሞላ ነው፡፡ ኮንቴይነሮቹ በቅርብ እንደመጡ ሰምቻለሁ፡፡ ድንኳኖቹ ግን ራሳቸው እርጅናቸውን ይመሰክራሉ፡፡ በተለይም በዚህ ያረጀ ድንኳን ውስጥ አጥንት ድረስ በሚገባውና ያገሬ ብርድ ማረኝ በሚያሰኘው የማልታ የክረምቱ ብርድ እንዴት ሆኖ ሊኖርበት እንደ ሚችል መድኃኔዓለም ይወቅ፡፡

በአሁኑ ጊዜ እዚህ መጠለያ የሚኖር አበሻ የለም፡፡ ሁሉም ጥለውት ወጥተው በየሥራቸው ተሠማርተዋል፡፡ እኔ ግን የታሪካችን አካል ነውና በቪዲዮ እና ፎቶ አስቀርቼዋለሁ፡፡

እንዲህ ተሰቃይተው እና መከራ ተቀብለው እዚህ ማልታ የደረሱት ሁሉ በአንድ ነገር ያስገርሙኛል፡፡ ሁሉም ለወላጆቻቸው እና ለእኅት ወንድሞቻቸው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ያዩትን መከራ ሳያዩ እዚያው በሀገራቸው ሊረዷቸው ደፋ ቀና ይላሉ፡፡ እንዲህ በመከራ ደርሰው ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ይልካሉ፡፡

ከዚህ በላይ ምን ደግነት አለ? የሚልኩት ገንዘብ እኮ የላብ ሳይሆን የደም ዋጋ ነው፡፡

Category:

Travel & Events

Tags:

License:

Standard YouTube License

  • likes, 0 dislikes

Link to this comment:

Share to:
see all

All Comments (0)

Sign In or Sign Up now to post a comment!
Loading...

Alert icon
0 / 00Unsaved Playlist Return to active list
    1. Your queue is empty. Add videos to your queue using this button:
      or sign in to load a different list.
    Loading...Loading...Saving...
    • Clear all videos from this list
    • Learn more